የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት አስተዳደር ሥርዓት ለማልማት የውል ስምምነት አደረጉ፡፡
· AI Solutions
EAII and Federal Auditor General Launch Digital Audit Management System
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በውል ስምምነቱ ወቅት እንደገለፁት ኢንስቲትዩቱ ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤቱን ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል ሥርዓት ለመዘርጋት ጥናት ሲደረግ እና ፍላጎት ሲለይ መቆየቱን ጠቁመው ሲስተሙ በተባለው ጊዜ እንደሚጠናቀቅ አረጋግጠዋል፡፡
የፌደራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ መሥሪያ ቤቱ በቴክኖሎጂ እንዲዘምን እና የፋይናንስ ኦዲትን በቴክኖሎጂ ለመምራት ስምምነቱ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የሚዘረጋው ሥርዓት አስተማማኝ እና ቀጣይነት እንዲኖረው በሀገር ልጆች የመሰራቱን ጠቀሜታ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረገው ስምምነት የፋይናንስ ኦዲት ሂደትን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ለማስተዳደር የሚያስችል ዲጂታል ሥርዓት ለማልማት ያለመ ነው፡፡ በዚህም የኦዲት እቅድና አፈፃፀም፣ የሰነድ አያያዝ፣ የሪፖርት ዝግጅት እና በኦዲተሮችና በተቋሙ መካከል ያለውን ትብብር በቴክኖሎጂ የሚደግፍ ሥርዓት ነው፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute