“ኤ.አይ ሰዎች ህልማቸዉን እንዲኖሩ ወሰን አልባ እድል የሰጠ ቴክኖሎጂ ነዉ።” ሺራዝ ሀሰን
· Visiting
Entrepreneur Sheeraz Hasan Praises Ethiopia’s AI Progress and Inspires Youth to Lead Africa’s Innovation Future
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ከመዝናኛዉ ኢንዱስትሪ ጋር በማዋሃድ የዘርፉ አንቀሳቃሽ እና ስራ ፈጣሪ የሆኑት ሺራዝ ሀሰን የኢትዮጵያን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጎብኝተዋል። ወጣቶች ስኬታማ የሆነ ህይወትን መመስረት የሚሹ ከሆኑ ራሳቸዉን ከአዳዲስ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ክህሎቶች ጋር በማላመድ ዘመኑ የሰጣቸዉን እድል ሊጠቀሙ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በጉብኝታቸው በኢንስቲትዩቱ ስላለዉ የኤ.አይ ምርምር፣ ልማት እና አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ቀርቦላቸዋል። በተቋሙ ያዩት ነገር በኢትዮጵያ ያለዉን የኤ.አይ ቴክኖሎጂ እድገት በጉልህ የሚያሳይ ነዉ ሲሉ ገልጸዉታል።
ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች ሀሳባቸውን ወደ ስኬታማ ንግዶች እንዲቀይሩ የሚያስችል ድጋፍ በማድረግ ላይ የሚገኘዉ የኤ.አይ ስታርታፕ ማዕከልም ምስጋና እንደሚገባዉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በዘርፉ ያለዉን ዓለም አቀፍ ፍላጎት ያማከለና በአፍሪካ ለቴክኖሎጂዉ ፈጠራ ግንባር ቀደም ማዕከል የመሆን ጠንካራ አቅም እንዳላት በጉብኝታቸዉ ማስተዋላቸዉን አብራርተዋል።
ሺራዝ ሀሰን ሆሊዉድ ዶት ኤ.አይ ፣ቦሊዉድ ዶት ኤ.አይ እና ሌሎችም የኤ.አይ ቴክኖሎጂን ከመዝናኛዉ ዘርፍ ጋር አጣምረዉ የሚሰሩ ኩባንያዎችን መስርተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute