“ኢትዮጵያ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ምን ያህል ርቀት መጓዟን ያየንበት ጉብኝት ነዉ።” የሳይበር ደህንነት ወር ላይ ለመሳተፍ የመጡ አፍሪካዊያን
· Visiting
International Cybersecurity Month Participants Visit EAII and Praise Ethiopia’s Homegrown AI Capabilities and Potential for African Cooperation
የ7ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር አህጉር አቀፍ ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝቱ ሀገሪቱ ቴክኖሎጂውንከማየት አልፋ በራሷ አቅም ለማልማት የምታደርገው ጥረትን ተገንዝበዋል።
ልዑካኑ የኢንስቲትዩቱን የኤ.አይ ዩኒፖድ ማዕከል፣ የሮቦቲክስ ወርክሾፕ እና የምርት ማሳያ ክፍሎች ጎብኝተዋል።ኢትዮጵያ በዘርፉ ያስመዘገበችውእድገት አፍሪካዊ ችግሮችን በራስ አቅም ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን ገልጸው፤ የተገነባውንም አቅም አድንቀዋል።
የኤ.አይ ቴክኖሎጂ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ካለው ፋይዳ ባሻገር የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ ያለው ወሳኝ ሚናም በጉብኝቱ ወቅት ተመላክቷል። ጉብኝቱ የአፍሪካ ሀገራት በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ልማት ልምድ የተለዋወጡበት እና የትብብር አቅጣጫዎችንየተገነዘቡበት ስኬታማ መድረክ ሆኗል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute