የደቡብ አፍሪካው ግዙፍ የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ በአፍሪካ የዳታ ማዕከላትን ሊገነባ ነው::
· Other
MTN Group and a UAE-backed investment platform have established Africa Data Hub Holding Limited to develop AI-ready data centres across Africa, initially focusing on South Africa and Nigeria.
የደቡብ አፍሪካው ግዙፍ የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ ኤምቲኤን (MTN Group) ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ በመተባበር “የአፍሪካ ዳታ ማዕከል ሆልዲንግ ሊሚትድ” የተሰኘ አዲስ ድርጅት መመስረቱን አስታውቋል። አዲሱ ተቋም በአፍሪካ ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፣ ለክላውድ (Cloud) እና ለድርጅቶች ዲጂታል አገልግሎቶች የሚያገለግሉ ዘመናዊ የዳታ ማዕከላትን በመገንባት ላይ ያተኩራል።በፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ የዳታ ማዕከላት በናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ይገነባሉ።ፕሮጀክቱ በሁለት ምዕራፎች የሚከናወን ነው፡፡ ጠቅላላ ወጪውም 240 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስ ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ የኤምቲኤን 2030 ራዕይ አካል ሲሆን በአፍሪካ የክላውድ አገልግሎቶች፣ የዳታ ማከማቻ እና የኮምፒውቲንግ አቅም ፍላጎት በፍጥነት እያደገ
መምጣቱን ተከትሎ የተጀመረ ነው። እንደ ዛላም አናሊቲክስ የገበያ ትንታኔ በአፍሪካ የክላውድ ገበያ በየዓመቱ ከ25 እስከ 30 በመቶ እያደገ ነው። የአፍሪካ የኤአይ ገበያ በ2025 ከነበረበት 4.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በ2030 ወደ 16.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያድግ ይገመታል።
ኤምቲኤን ፕሮጀክቱን በናይጄሪያ እና በደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳይገድብ ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገራትም ለማስፋፋት ማቀዱን ገልጿል። ይህም ኩባንያው ከነባር የቴሌኮም አገልግሎቶች ወደ ክላውድ፣ ዳታ እና የድርጅርጅት ዲጂታል አገልግሎቶች ለመሸጋገር እየወሰደ ያለው እርምጃ አካል ነው።
የኤምቲኤን አዲሱ ፕሮጀክት በአፍሪካ የኤአይ ልማትን የሚደግፉ መሠረተ ልማቶችን በማጠናከር የኮምፒውቲንግ አቅምን፣ የዳታ ማከማቻን እና የክላውድ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute