አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የፋይናንስ የሥራ ሂደቶችን እያዘመነ ነው፡፡
· AI Solutions
Advanced multimodal AI models like Gemini 3.1 Pro are transforming financial workflows by improving document analysis accuracy and accelerating data processing in financial institutions.
የፋይናንስ ተቋማት ውስብስብ የሥራ ሂደቶቻቸውን ለማከናወን የላቁ ባለብዙ አገልግሎት የኤ.አይ ሞዴል ( Multimodal AI) ቴክኖሎጂዎችን በስፋት እየተጠቀሙ ይገኛሉ። ቀደም ሲል የነበሩ መደበኛ የሰነድ ንባብ ሥርዓቶች(OCR) እንደ ሰንጠረዦች እና የተነባበሩ መረጃዎችን በትክክል መለየት ይሳናቸው ነበር::
አሁን ግን እንደ Gemini 3.1 Pro ያሉ የኤ.አይ ሞዴሎች ሰነዶችን የመረዳት የላቀችሎታ ስላላቸው ይህንን ችግር መቅረፍ እየቻሉ ነው።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ይህ አዲሱ የኤ.አይ አቀራረብ ካልተደራጁ ጥሬ ሰነዶች ላይ መረጃን የመለየት ብቃትን ከ 13 እስከ 15 በመቶ አሻሽሏል። በተለይ ጥቅጥቅ ያሉ የፋይናንስ ቃላትና ውስብስብ ሰንጠረዦች የሚገኙባቸው የሂሳብ መግለጫዎችን በቀላሉ ለመተንተን አስችሏል።
የሥራ ሂደቱ ውጤታማ ከሚያደርጉት ሞዴሎች መካከል Gemini 3.1 Pro እና Gemini 3 Flash ተጠቃሽ ናቸው፡፡ Gemini 3.1 Pro ውስብስብ የሰነድ ቅርጾችን ሲተነትን፤ Gemini 3 Flash ደግሞ ፈጣን ማጠቃለያዎችን ያመነጫል። ይህ ጥምረት የሥራ መዘግየትን በመቀነስ ተቋማት ከፍተኛ መጠን ያላቸውን መረጃዎች በአጭር ጊዜ እንዲያከናውኑ ይረዳቸዋል።
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኒውስ እንደዘገበው የፋይናንስ ዘርፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ በመሆኑ፤ ተቋማት የኤ.አይ ውጤቶችን ለሥራ ከመጠቀማቸው በፊት ደግመው ማረጋገጥ እንዳለባቸውና ጥብቅ የቁጥጥር ደንቦችን መከተል እንደሚገባቸው ባለሙያዎች ያሳስባሉ።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute