ኤጅ ኤ.አይ (Edge AI) ምንድን ነው?
· Study Shows
Edge AI enables real-time intelligence by processing data directly on devices without relying on the cloud.
ኤጅ ኤ.አይ ማለትየአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስልተ-ቀመሮች (Algorithms) በቀጥታ በመሣሪያው ላይ ማለትም በስልክ፣ በካሜራ፣ በሴንሰር፣ በሮቦት ወይም በአይ.ኦ.ቲ መሣሪያዎች ላይ አሁናዊ የዳታ ማቀናበር እና ትንተናን የሚከውኑበት መንገድ ነው፡፡ ይህም በክላውድ መሠረተ ልማቶች ላይ ጥገኛ ከመሆን ይልቅ የዳታ ማቀናበር እና ትንተናው እዛው መሣሪያው ላይ የሚጠናቅቀበት ሂደት ነው፡፡
በተለመደውየኤ.አይ አሠራር መረጃ ተሰብስቦወደ ማዕከላዊ የክላውድ ሰርቨር ይሄዳል፡፡ በመቀጠልም አስፈላጊው ትንታኔ ተደርጎለት መልሱ ወደ ስርዓቱይላካል። ኤጅ ኤ.አይ ግን ይህንን ጉዞ ያስቀራል። "ኤጅ" የሚለውም ቃል መረጃውየሚመነጭበትን ጫፍ ወይም ምንጭያመለክታል።
በአይ.ቢ.ኤም መረጃ መሠረት ኤጅ ኤ.አይ ቅጽበታዊ ምላሽ በመስጠት፣ የግል ሚስጥር ጥበቃን በማጠናከር፣ እንደ አስፈላጊነቱ በኢንተርኔት ወይም ያለኢንተርኔት በመስራት እና ወጪን በመቀነስ ከፍ ያለ ጠቀሜታ እየሰጠ ይገኛል፡፡
በጤናውዘርፍ ኤጅ ኤ.አይበታካሚው አቅራቢያ ባሉ መሣሪያዎች አማካኝነት ፈጣን ውሳኔለመስጠት ይረዳል። እንዲሁም በግብርናው ዘርፍ በተለይ ኢንተርኔት በማይደርስባቸው አካባቢዎች ኤጅ ኤ.አይ ትልቅ ለውጥያመጣል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute