የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለሴት አመራሮቹ ስልታዊ አመራር እና አስተዳደር ላይ ያተኮረ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡
· Education
EAII Launches Leadership Training Program to Empower Female Executives with Strategic and Transformational Management Skills.
ኢንስቲትዩቱ ለሴት አመራሮቹ ለሦስት ቀናት የሚቆይ የአቅም ማጠናከሪያ ስልጠና በዛሬው ዕለት መስጠት ጀምሯል፡፡ ስልጠናው በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የአካዳሚው ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መሰረት ደስታ ናቸው፡፡ ወ/ሮ መሰረት በንግግራቸው እንደገለጹት የተዘጋጁት ስልጠናዎች በፍጥነት ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም ውስጥ የሴቶችን የመሪነት አቅም እና ችሎታ ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ሴት አመራሮች ህዝብን በእውቀት እና በዓላማ ለመምራት እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች አቅም የሚፈጥሩ ናቸው ብለዋል፡፡
ስልጠናው ተቋማዊ አመራር፣ የለውጥ አመራር እና የለውጥ አስተዳደር እንዲሁም ስልታዊ አመራር እና አስተዳደር ላይ ትኩረታቸውን ያደርጋሉ፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute