ደቡብ ኮሪያ የራሷን የኤአይ ሞዴል ለመገንባት ከፍተኛ ገንዘብ መደበች
· AI Investment
South Korea Invests Billions to Build Sovereign AI and Strengthen Technological Independence
ደቡብ ኮሪያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በሴሚኮንዳክተር እና በዳታ ማዕከላት ዘርፎች ያላትን አቅም ለማጠናከር ትልቅ የበጀት እቅድ ይፋ አድርጋለች።
ፕሬዚዳንት ሊ ጄ-ሚዩንግ እንዳስታወቁት ከሀገሪቱ በጀት ውስጥ 21.3 ትሪሊዮን ዎን (ከ15 ቢሊዮን ዶላር ) የኤአይ ቴክኖሎጂን ለማሳደግ ይውላል።
ከዚህ በተጨማሪ ሀገሪቱን ተወዳድሪ ለማድረግ የራሷን"ሉዓላዊ የኤአይ ሞዴል" ለመገንባት 4.6 ትሪሊዮን ዎን ለመመደብ አቅዳለች። ሉዓላዊ ኤአይ ማለት
አንድ ሀገር በራሷ ቋንቋ፣ ባህልና መረጃ ላይ ተመስርታ የምታለማውና የምትቆጣጠረው የኤአይ ሥርዓት ነው። ደቡብ ኮሪያ በውጭ ሀገር ቴክኖሎጂዎች ላይ
ያላትን ጥገኝነት ቀንሳ የቴክኖሎጂ ነጻነቷን በማጠናከር በዓለም የኤአይ ውድድር ውስጥ ተፎካካሪ ለመሆን ትፈልጋለች።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute