የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራርና ሰራተኞች ደም በመለገስ ማህበራዊ አጋርነታቸውን አረጋገጡ
· Other
EAII leaders and staff participated in a blood donation campaign, reinforcing the Institute's commitment to social responsibility, volunteerism, and community well-being alongside its mission to advance artificial intelligence and digital innovation.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ሰራተኞች በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ በተዘጋጀ መርኃግብር ላይ በመገኘት ደም ለገሱ።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ተቋሙ በቴክኖሎጂው ዘርፍ እያከናወነ ከሚገኘው ሀገራዊ ተልዕኮ ጎን ለጎን ህብረተሰባዊ ኃላፊነቱን በላቀ ቁርጠኝነት ለመወጣት ምንጊዜም ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ የደም ልገሳ መርኃግብርም የዚሁ ሰብዓዊና ማህበራዊ አጋርነት ማሳያ አካል መሆኑን አብራርተዋል። ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ተቋሙ በሰብዓዊ ድጋፍና በማህበራዊ ልማት ዘርፎች የጀመራቸውን አዎንታዊ ተሳትፎዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።
የኢንስቲትዩቱ አመራሮች እና ባለሙያዎች መሰል በጎ ተግባራትን በየጊዜው በማከናወን የዜግነት ኃላፊነታቸውን የመወጣት መልካም ባህልና ልምድ ማዳበራቸው ይታወሳል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute