ኤ.አይ የኢኮኖሚና የአኗኗር ሥርዓትን እያዘመነ ነው::
· AI Solutions
Google Research has introduced the Planetary Prediction Engine, an AI-powered system that automates geospatial data discovery, model development and forecasting to help predict food security, public health, environmental and socio-economic risks.
ጉግል የምድር ገጽታ መረጃዎችን በመጠቀም የህዝብ ጤና፣ የምግብ ዋስትና፣ የአካባቢ አደጋ እና ማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ለመተንበይ የሚያስችል “ፕላኔታዊ ትንበያ ሞተር” (Planetary Prediction Engine - PPE) የተሰኘ ቴክኖሎጂ አስተዋውቋል። ቴክኖሎጂው ከተፈጥሯዊ ቋንቋ ትዕዛዝ በመነሳት የጂኦስፓሻል መረጃን ከመፈለግና ከማጽዳት ጀምሮ የመረጃ ባህሪያትን ማዘጋጀት፣ ሞዴሎችን ማሰልጠን፣ ውጤታቸውን መገምገም እና የትንበያ ሪፖርት ማዘጋጀት ድረስ ያሉ ሂደቶችን በራሱ ያከናውናል።
በተለይም ቀጠናዊ የምግብ ዋስትና ሁኔታ መተንበይ፣ የተፈጥሮ አደጋዎችን መገመት፣ የበሽታ ወረርሽኞችን መከታተል እና ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጋላጭነትን ለመለየት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ይህ ቴክኖሎጂ በሦስት ዋና ዋና ደረጃዎች ይሠራል። በመጀመሪያ ተገቢውን የጂኦስፓሻል መረጃ በራሱ ይፈልጋል፤ በመቀጠል የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን በማጣመር ለትንበያ የሚያገለግል የመረጃ ስብስብ ያዘጋጃል፤ በሶስተኛ ደረጃም የተለያዩ የማሽን ለርኒንግ ሞዴሎችን በመፈተሽ ትንበያውን ያዘጋጃል።
ሥርዓቱ ከGoogle Earth Engine እና Data Commons ከመሳሰሉ የጂኦስፓሻል መረጃ ማዕከሎች መረጃ ከማግኘቱ በተጨማሪ፤ በእነዚህ ምንጮች የማይገኝ መረጃ ሲያስፈልግ ከድረ ገጽ ላይ በመፈለግ፣ ከመንግሥታዊ ፖርታሎችና ከአካዳሚክ ምንጮች መረጃ ሊሰበስብ ይችላል። ለመረጃ ማጣራትና ሞዴል
ለመገንባት ሳምንታት ይፈጅ የነበረውን ሥራ የፕላኔታዊ ትንበያ ሞተር ወደ ጥቂት ደቂቃዎች ሊያሳጥረው ይችላል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute