ሳይንቲስቶች በዘር የሚተላለፉ በሽታዎችን የጄኔቲክ አደጋ ለመተንበይ የሚያስችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስርአት ፈጠሩ፡፡
· Machine Learning
የአሜሪካ ተመራማሪዎች ያልተለመዱ በዘረመል ቅደም ተከተል ላይ የሚደረጉ ለውጦች ወደ በሽታ ያመሩ እንደሆነ ለመተንበይ የሚያስችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስርዓት ፈጥረዋል፡፡
በኒውዮርክ የሚገኙ ተመራማሪዎች በታካሚዎች የጤና ታሪክ መረጃ እና በዘር የሚተላለፍ በሽታ ስጋታቸው ላይ ተመስርተው በበሽታ ሊያዙ እንደሚችሉ ለመተንበይ የሚያስችል የኤ.አይ እና የኤሌክትሮኒክስ የህክምና መዝገቦችን የሚጠቀም መሳሪያ ፈጠረዋል፡፡
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሞዴሉ ዶክተሮች የዘረመል ምርመራ ውጤቶችን እንዲረዱ እና ለታካሚዎች ተገቢውን የእንክብካቤ ደረጃ እንዲያውቁ ይጠቅማል።
የጄኔቲክ ምርመራው በሰው ዘረመል (ዲ.ኤን.ኤ) ውስጥ ለውጦችን በመለየት በሰዎች ጤና ላይ ትንሽ ወይም ምንም ተጽእኖ የሌላቸውን ነገሮች ለመለየት ያስችላል፡፡
እንደ ዩሮ ኒውስ ዘገባ ተመራማሪዎቹ በፈጠሩት ሞዴል አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን እና የላቦራቶሪ መረጃን በመጠቀም በዘረመል ምርመራ የኮሊስትሮል መጠንን ወይም የደም ብዛትን የመሳሰሉ በሽታዎችን ጨምሮ ሌሎች በሽታዎችንም ለመተንበያ ያስችላል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute