የንብ ባንክ የሥራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ
· Visiting
#EAII #NibBank #ArtificialIntelligence #FinTech #Innovation
የንብ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሥራ ጉብኝት አደረጉ።
ለባንኩ የሥራ ኃላፊዎች የኢንስቲትዩቱ የዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የቴክኖሎጂ አማካሪ ሻምበል ይልማ (ዶ/ር) ገለጻ አድርገውላቸዋል። በገለጻቸውም
ኢንስቲትዩቱ የኤ.አይ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የማኅበረሰቡን ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን አስረድተዋል። ከጉብኝቱ ጎን ለጎንም ተቋማቱ በቀጣይ አብረው መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል።
የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች በኢንስቲትዩቱ የተመለከቷቸው የፈጠራ ሥራዎች እንዳስደነቋቸው ገልጸው፤ ተቋሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸው ተግባራት የሚያስመሰግኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በውይይቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ የሥራ ኃላፊዎች እንደገለጹት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዓለም ገና ሙሉ በሙሉ ያልተረዳው አዲስና በፍጥነት ተለዋዋጭ የሆነ ቴክኖሎጂ ነው። ኢንስቲትዩቱ ብሔራዊ ፖሊሲ አዘጋጅቶና መሠረታዊ የኤ.አይ መመሪያዎችን ቀርጾ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። አክለውም የቴክኖሎጂውን ፍጥነትና ተለዋዋጭነት ባገናዘበ መልኩ በፋይናንስ ዘርፉ የሚያገለግሉ የቻትቦት ቴክኖሎጂዎችን ማበልጸግ መቻሉን አብራርተዋል።
የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ሀገር በቀል ቋንቋዎችን ለማሽን ለማስተማር ያከናወናቸውን ሥራዎች አድንቀዋል። በቀጣይም በፋይናንስ
ዘርፍ በቻትቦት አጠቃቀም እንዲሁም በስታርት አፕ ዙሪያ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ለመሥራት ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute