የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ለይዘት ፈጠራ እድገት ያለውን ፋይዳ የሚዳስስ የፓናል ውይይት ተካሄደ
· Other
AI and Digital Creators Discuss Ethical Content Innovation at Africa’s Influencers Summit to Strengthen Creativity and Digital Productivity
በአድዋ ድል መታሰቢያ "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው የመጀመሪያው የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS-2026) ላይ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በይዘት ፈጠራ ላይ ያለውን ሚና የሚዳስስ የፓናል ውይይት ተካሄደ።
በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች እና በመላው አፍሪካ ከፍተኛ ተከታይ ያላቸው ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ ቴክኖሎጂው ፈጠራ የታከለባቸው ይዘቶችን ከመቅረጽ ባለፈ ስራዎች የሚከናወኑበትን ፍጥነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምር ተመላክቷል። ይሁን እንጂ፣ ከቴክኖሎጂው ጋር ተያይዘው የሚመጡ ስጋቶችን ለመከላከል አጠቃቀሙን ስነ-ምግባራዊ በሆነ መንገድ መምራትና በፖሊሲ መደገፍ ወሳኝ መሆኑ በስፋት ተነስቷል።
ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa) ከኤ.ጂ.ኤ (AGA) የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ፣ ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። ውይይቱ አህጉሪቱ በዲጂታል ዘርፍ ያላትን አቅም ለማሳደግና የኤ.አይ ቴክኖሎጂን ለበጎ ተግባር ለማዋል አዲስ አቅጣጫ ጠቋሚ መሆኑ ተገልጿል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute