የኤ.አይ ቺፕ አምራቹ ኤችድ ኩባንያ የገበያ ዋጋ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ በእጥፍ አደገ፡፡
· AI Investment
AI chip startup Etched has doubled its valuation to $21 billion after raising $700 million in a Jane Street-led funding round, highlighting growing investor demand for specialized and cost-efficient AI inference infrastructure.
በጄንስትሪት የንግድ ድርጅት የሚደገፈው ኤችድ (Etched) የተባለው የኤ.አይ ቺፕ አምራች ኩባንያ ባለሀብቶች ለልዩ የኤ.አይ ሞዴል ልማት ቺፖች ባላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ምክንያት የገበያ ዋጋው በአንድ ወር ባልሞላጊዜ ውስጥ ከእጥፍ በላይ በማደግ 21 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን አስታውቋል።
በካሊፎርኒያ ሳንሆዜ የሚገኘው ይህ ኩባንያ 700 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ የኢንቨስትመንት ገንዘብ የሰበሰበ ሲሆን ቀደም ሲል ድጋፍ ሲያደርግለት የነበረው ጄን ስትሪት የገንዘብ ማሰባሰቡን በግንባር ቀደምትነት መርቶታል፤ በተጨማሪም ክላይነር ፐርኪንስ፣ ሴኮያ፣ አንድሪሰን ሆሮዊትዝ እና ታይገርግሎባል የተባሉ የኩባኛው ደጋፊ ተቋማት ተሳትፈዋል።
ይህየገንዘብ ድጋፍ ባለሀብቶች የኤ.አይ ሞዴሎችን ለማልማት በሚያስፈልጉ መሠረተ-ልማቶች ላይ ያላቸው ፍላጎት መጨመሩን ያሳያል። በተለይም ኢንፈረንስ ማለትም የሰለጠኑ የኤ.አይ ሞዴሎችን በመጠቀም ምላሾችን የማፍራት ሂደት ፍላጎቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል።
ኤችድየኤ.አይ ሞዴሎች በፍጥነት እና በአነስተኛ ወጪ እንዲሠሩ የሚያስችሉ ልዩ የኤ.አይኢንፈረንስ ሥርዓቶችን የሚገነባ ሲሆን፤ በኤ.አይ ቺፕ ገበያ ውስጥ የኢንቪዲያን የበላይነት ለመፎካከር እየጣሩ ካሉ አዳዲስኩባንያዎች አንዱ ሆኗል።
እንደ ሮይተርስ ዘገባ ኤችድ ባለፈውሐምሌ ወር በተደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ ወቅት የገበያ ዋጋው 10.3 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን፤ ከመንግሥታዊ እና ከግል የኤ.አይ ኩባንያዎች እንዲሁም ከክላውድ አገልግሎት አቅራቢዎች ጋር ከ1 ቢሊዮንዶላር በላይ የሚያወጡ የውል ስምምነቶችን አድርጓል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute