ለጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ክበብ አባላት ተማሪዎች የኤ.አይ የግንዛቤ ስልጠና ተሰጠ፡፡
· Education
EAII Provides AI Awareness Training to Inspire Digital Skills, Innovation, and Future Tech Leadership Among Students
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጥቁር አንበሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላቋቋመው የኤ.አይ (AI) ክበብ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ
ስልጠና ተሰጥቷል።
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የተማሪዎችን እውቀት ለማሳደግ እና የቴክኖሎጂውን አቅም በአግባቡ እንዲረዱ ለማስቻል በተዘጋጀው በዚህ ስልጠና፤ መሰረታዊ የኤ.አይ ጽንሰ-ሀሳቦች በስፋት ተዳሰዋል። ስልጠናው ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምንነት ጀምሮ፣ የማሽን ለርኒንግ እና የፕሮግራሚንግ ሚና፣ የቴክኖሎጂው
የአሰራር ሂደት፣ እንዲሁም የስነ ምግባራዊ ኤ.አይ ፋይዳ ላይ ያተኮረ ነው።
በስልጠናው የተሳተፉ የክበቡ አባላት ስልጠናው የቴክኖሎጂውን አስፈላጊነት የተረዱበት ስለመሆኑ ተናግረዋል። ተማሪዎቹ ያገኙትን መሰረታዊ እውቀት በመጠቀም ለወደፊት በችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎች ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ እና ለዘርፉ ስኬት አስፈላጊ በሆኑ የትምህርት ዓይነቶች ላይ ልዩ ዝንባሌ እንደሚያሳድሩ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ተማሪዎችን በቴክኖሎጂው ዘርፍ ብቁ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያደርገውን ተከታታይ የድጋፍና ስልጠና መርሃ ግብር በመላ አገሪቱ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute