ኢትዮጵያ እና ጆርዳን በቴክኖሎጂ እና በዲጂታል ሽግግር መስኮች በትብብር እንደሚሰሩ ተገለጸ
· Visiting
Jordan’s Ambassador to Ethiopia and Permanent Representative to the African Union, Amjad Al-Momani, visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to discuss cooperation in artificial intelligence, digital transformation, capacity building, and experience sharing.
በኢትዮጵያ የጆርዳን ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እንዲሁም በአፍሪካ ኅብረት የጆርዳን ቋሚ መልዕክተኛ አምጃድ አል ሞውማኒ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) አምባሳደሩን በኢንስቲትዩቱ ተቀብለው አነጋግረዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ አገር አቀፍ የቴክኖሎጂ ልማትን ለማፋጠን የሚያከናውናቸውን የሥራ እንቅስቃሴዎች እና የቴክኖሎጂ ልማት ሥራዎች አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ጉብኝቱን አስመልክቶ ሀሳባቸውን የሰጡት አምባሳደር አምጃድ አል ሞውማኒ፤ ኢትዮጵያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መስክ የያዘችው ራዕይና እያስመዘገበችው ያለው እድገት አበረታች መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም የኢንስቲትዩቱ ሥራዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በፈጠራ ላይ የተመሰረተ ልማትን እውን ለማድረግ ካላቸው አርቆ አሳቢ ራዕይ ጋር ፍጹም የሚስማሙ መሆናቸውን በአድናቆት አንስተዋል። አምባሳደሩ ለተደረገላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበው፤ ጆርዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ወዳጅነት ይበልጥ ለማጠናከር እና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በአቅም ግንባታ እንዲሁም በልምድ ልውውጥ ዘርፎች የሁለቱን አገራት ትብብር አጠናክሮ ለመቀጠል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute