ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተዉጣጡ ልዑካን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።
· Visiting
Multi-Sector Delegates Visit EAII to Explore AI Innovation for National Productivity, Capacity Building, and Economic Growth.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና(ዶ/ር) ሀገር ከኤ.አይ ቴክኖሎጂ የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ በመከናወን
ላይ ያሉ ተግባራትን ለልዑካኑ አብራርተዋል። ልዑካኑ በጉብኝቱ የቀሰሙትን ልምድ በሚሳተፉበት የስራ ዘርፎች ተግባራዊ እንዲያደርጉም አደራ ብለዋል።
ጉብኝቱን አስመልክቶ ሀሳባቸዉን ያጋሩ የልዑካኑ አባላት ሀገራችን በዓለማቀፉ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ የዉድድር ሜዳ ምን ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ያመላከተ ጉብኝት መሆኑን ገልጸዋል። ኢንስቲትዩቱ ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚለሙበትና ለትዉልድ የሚተላለፍ አቅም ያለበት ስፍራ መሆኑንም ጠቁመዋል። ልዑካኑ በኢንስቲትዩቱ ያዩትን ቴክኖሎጂ በተሰማሩበት የተለያየ የስራ መስክ ላይ ተግባራዊ ማድረግ ቢቻል የተሻለ አቅም መፍጠር እንደሚቻል ያላቸዉን ተስፋ አስታዉቀዋል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት በኢንስቲትዩቱ የሚገኙ የኤ.አይ ስታርታፕ ማዕከል፣ የሮቦቲክስ ወርክሾፕ፣ የምርት ማሳያ ክፍሎች እንዲሁም ዲጂታል ቤተ መጽሀፍትን ጎብኝተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute