የኤአይ ኢንቨስትመንት ከዳታ ማዕከላት ግንባታ በላይ መሻገር እንዳለበት ተገለጸ
· AI Investment
World Investment Forum Urges Broader AI Investment to Support Inclusive Digital Development
በኳታር ዶሃ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ኢንቨስትመንት ፎረም (World Investment Forum 2026) ላይ የኤአይ ኢንቨስትመንት ከዳታ ማዕከላት
ግንባታ አልፎ የኢንተርኔት አቅርቦት፣ የኃይል አቅርቦት፣ የምርምር ሥራዎች እና የሰው ኃይል ክህሎትን ያካተተ መሆን እንዳለበት ተጠቆመ።
የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባኤ (UNCTAD) ሪፖርት እንደሚያሳየው በኤአይ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚደረግ አዲስ ኢንቨስትመንት በዓመት በአማካይ 47 በመቶ እያደገ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅትም ከጠቅላላ አዲስ ኢንቨስትመንት ውስጥ 60 በመቶውን ይዟል።
አሁን ላይ የበለጸጉ ሀገራት እና 100 ግዙፍ ኩባንያዎች የዓለም አቀፉን የኤአይ ምርምርና ልማት 40 በመቶ ተቆጣጥረውታል። የተባበሩት መንግሥታት
የንግድና ልማት ጉባኤ ከዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት ጋር በመተባበር ታዳጊ ሀገራት ከኤአይ ዲጂታል መሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት እና የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute