“አፍሪካን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማላቅ” በሚል መሪ ቃል በበይነመረብ እየተካሄደ የሚገኘው አራተኛው ፓንአፍሪኮን ኤ.አይ 2025 የመጀመሪያ ቀን ውሎ ተጠናቀቀ።
· AI Solutions
“Day One Highlights Global Expertise and Breakthrough Research in AI and NLP”
በኮንፍራንሱ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂው ተመራማሪዎች ተሳትፈውበታል። ከእነዚህም መካከል ከሃውክ አፕላይድ ሳይንስ እና አርትስ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር አኪም ኢበንታል እና ከኡልም ዩኒቨርሲቲ የኒውራል ኢንፎርሜሽን ፕሮሰሲንግ ኢንስቲትዩት ፕሮፌሰር ፍሪድሄልም ሽቬንከር የመክፈቻ ንግግሮችን አቅርበዋል።
በመጀመሪያው ቀን በአጠቃላይ 20 አዳዲስ የምርምር ጽሑፎች ቀርበዋል። እነዚህም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ትግበራ እና በተፈጥሮ ቋንቋ ቅንብር ላይ ያተኮሩ ናቸው። እነዚህ ስራዎች ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች እና በሌሎች የዘርፉ ተመራማሪዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የፓንአፍሪኮን ኤ.አይ ኮንፍራንስ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በየዓመቱ የሚዘጋጅ ሲሆን፣ የአፍሪካ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተመራማሪዎች የጥናት ውጤቶቻቸውን የሚያቀርቡበት እና ትብብር የሚፈጥሩበት መድረክ ነው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute