ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ስታርታፖች የተሰጠው የቡት ካምፕ ስልጠና የማጠቃለያ መርሃ ግብር ተካሄደ።
· Education
AI Bootcamp Training for University Students and Startups in Ethiopia Focuses on Practical Innovation and Scalable Solutions
ስልጠናው በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ዩ.ኤን.ዲ.ፒ ትብብር በተዘጋጀው የኤ.አይ ዩኒፖድ የፈጠራ ማዕከል የተሰጠ ነው።
በማጠቃለያ መርኃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የፈጠራ ስራዎችን ከማልማት ባሻገር ወደ ተግባር በመለወጥ ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባ ገልጸዋል። ኢንስቲትዩቱ በቴክኖሎጂው ላይ የሚሰሩ የግል ዘርፍ አንቀሳቃሾችን ማበረታታት ላይ ወደፊትም በስፋት እንደሚሰራ ዋና ዳይሬክተሩ አመላክተዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስታርታፕ ማዕከል ኃላፊ ልብሰወርቅ ነጋሽ (ዶ/ር) በበኩላቸው የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን አልሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር የኤ.አይ ዩኒፖድን የመሰሉ ማዕከላት ወሳኝ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ሰልጣኞች ሀሳባቸውን ወደ ተግባር መለወጥ የሚያስች ክህሎት በስልጠናው በማግኘታቸው ዕድሉን በሚገባ እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል።
ለአስራ አንድ ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና የኤ.አይ ቴክኖሎጂ መሰረታዊ ግንዛቤን እና ስታርታፖች ቴክኖሎጂውን በመጠቀም የፈጠራ ስራቸውን ወደ ገንዘብ እንዲቀይሩ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር።
ስልጠናውን ሲከታተሉ ለነበሩ ሰልጣኞች እና አሰልጣኞች የእውቅና የምስክር ወረቀት በመርኃ ግብሩ ላይ ተበርክቷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute