ኦፕን ኤ.አይ ከጉግል ጋር ለመወዳደር የሚያስችለው አዲስ ብራውዘር ይፋ አደረገ፡፡
· Other
OpenAI Launches ChatGPT Atlas Browser for Mac, Redefining Web Search with Built-In AI and Challenging Google Chrome’s Dominance.
ኦፕን ኤ.አይ ኩባንያ ጉግልን እና መሰል ተወዳዳሪዎችን ለመገዳደር የሚያስችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አቅም የተቸረው አዲስ የድረ-ገጽ አሳሽ (ብራውዘር) ይፋ አድርጓል።
ቻት ጂፒቲ አትላስ የተባለው ይህ አሳሽ በፍለጋ ውስጥ ቁልፍ ሚና የነበረውን የአድራሻ መከተቢያ አስቀርቷል።
የአትላስ መምጣት ኦፕን ኤ.አይ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ላይ ላዋለው ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ አዲስ ገቢ መፍጠሪያ መንገዶችን ለመፈለግ እና እያደገ የመጣውን የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት በሚጥርበት ወቅት ነው ተብሏል።
ኦፕን ኤ.አይ ተጠቃሚዎችን ወደ ኦንላይን አገልግሎቶቹ ለመሳብ የተለያዩ አዳዲስ ጥረቶችን እያደረገ ነው፡፡ እንደ ሾፒፋይ፣ ኤክስፒዲያ እና ቡኪንግ ዶት ኮምን ከመሰሉ የበይነ መረብ አገልግሎቶች ጋር በመተባበር እየሰራ ነው ሲል ቢ.ቢ.ሲ አስነብቧል።
ኩባንያው አዲሱን አሳሽ ለጊዜው በአፕል ማክኦኤስ (MacOS) ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ ብቻ አገልግሎት እንዲሰጥ አድርጓል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute