የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በሀዋሳ ከተማ ለሚገኙ የኤ.አይ ክበብ አባላት ስልጠና ሰጠ።
· Education
EAII Expands AI Training in Hawassa to Build Digital Skills, Future Talent, and Innovation Capacity
በስልጠናው የማሽን ለርኒንግ፣ ጀነሬቲቭ ኤ.አይ፣ፕሮግራሚንግ እና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መሰረታዊ ክህሎቶች የተዳሰሱ ሲሆን፤ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብደረጃ የቀሰሙትን እውቀት በተግባር እንዲለማመዱ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። በኢንስቲትዩቱ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና በሀዋሳ ከተማ ለሚገኘው አላሙራ ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት ለሚማሩ የኤ.አይ ክበብ አባላት ነው የተሰጠው።
የአላሙራ ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት ርዕሰመምህር አቶ ደጀኔቃሊሞ ስልጠናው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይን ዕውን ለማድረግ የሰለጠነ የሰውኃይል የማፍራት ግብን ከማሳካት አንጻር ጉልህ ሚናእንዳለው ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ በመላ ኢትዮጵያ ባቋቋማቸው የኤ.አይክበቦች አማካኝነትተመሳሳይ ስልጠናዎችንበመስጠት ላይ ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴታዳጊዎች ከቴክኖሎጂ ጋር ያላቸውን ቁርኝት በማሳደግ ሀገር ተረካቢ ብቁትውልድን ለመገንባትየሚያስችል መሰረት እየጣለ ይገኛል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute