ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ያለው ሚና የማይተካ መሆኑ ተገለጸ።
· Other
EAII and Addis Ababa University Launch Research and Innovation Week to Advance Digital Transformation and Innovation-Driven Growth
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ፈጠራ ሳምንትን በጋራ እያካሄዱ ነው፡፡ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና በላቁ ቴክኖሎጂዎች መካከል ያለውን ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመው ዓመታዊው የምርምርና ፈጠራ ሳምንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት መካሄድ ጀምሯል።
በትምህርት፣ ምርምር እና ዲጂታላይዜሽን ፈጠራን እና የኢንዱስትሪ ትስስርን ማሳደግ ላይ ባተኮረው በዚህ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ቁልፍ ተዋናይ በመሆን በመሳተፍ ላይ ይገኛል። የኢንስቲትዩቱ የዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የቴክኖሎጂ አማካሪ ሻምበል ይልማ (ዶ/ር) ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ያለውን የማይተካ ሚና በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል። ኢንስቲትዩቱ በየደረጃው የኤ.አይ ክበባትን በማቋቋም የወደፊት ባለሙያዎችን እያፈራ እንደሚገኝና ለስታርታፖች አስፈላጊውን የቴክኒክና የመሰረተ ልማት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ችግር ፈቺ ምርምሮች ላይ ትኩረት ማድረጉን በመጥቀስ፤ ተማሪዎችና ተመራማሪዎች ለሀገር እድገት ወሳኝ በሆኑ የፈጠራ ስራዎችና የኢንዱስትሪ ትስስር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
በኢንስቲትዩቱ፣ በዩኒቨርሲቲውና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ትብብር የተዘጋጀው ይህ መድረክ የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ሽግግር በሚያፋጥኑ ውይይቶች ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት ይቆያል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute