ቻት ጂፒቲን በሳምንት 800 ሚሊዮን ሰዎች እየተጠቀሙት መሆኑ ተነገረ
· AI Investment
የOpenAI የChatGPT ተጠቃሚዎች በሳምንት 800 ሚሊዮን ደርሰዋል::
የኦፕን ኤ.አይ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳም አልትማን እንዳስታወቁት ሸማቾች፣ አበልጻጊዎች፣ ኢንተርፕራይዞችና መንግሥታት ቻት ጂፒቲን ከስራቸው ጋር በማዋሀድ እየተጠቀሙበት ነዉ፡፡
ሳም አልትማን በቻት ጂፒቲ ላይ አዳዲስ መተግበሪያዎች ለማካተት በተዘጋጀ መድረክ ላይ እንደተናገሩት በአሁኑ ጊዜ 4 ሚሊዮን አበልጻጊዎች ከኦፕን ኤ.አይ ጋር ይሰራሉ፡፡ ከ800 ሚሊዮን በላይ ሰዎችም በየሳምንቱ ቻት ጂፒቲን ይጠቀማሉ ብለዋል፡፡ እንዲሁም በደቂቃ ከ6 ቢሊዮን በላይ ጥያቄዎች ወደ ቻት ጂፒቲ እንደሚላኩም ጠቁመዋል፡፡
እ.ኤ.አ. በኖቬምበር 2022 ስራ የጀመረው ቻት ጂፒቲ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የተጠሚቃዎች ዕድገት እያሳየ ሲሆን ይህም ከሌሎች የኤ.አይ መተግበሪያዎች በበለጠ ፍጥነት እያደጉ ካሉ አገልግሎቶች አንዱ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
እንደ ቴክ ክረንች ዘገባ በአሁኑ ጊዜ ኩባንያው 500 ቢሊዮን ዶላር ሀብት አለዉ፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute