የኤአይ ተደራሽነት ክፍተትን ለማጥበብ 3 ቢሊዮን ዶላር የዓለም አቀፍ ፈንድ ጥሪ ቀረበ
· Other
UN Proposes a $3 Billion Global Fund to Expand Equitable AI Access and Strengthen Developing Countries’ Technological Capabilities
የተባበሩት መንግሥታትታዳጊ ሀገራት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በፍትሃዊነት እንዲጠቀሙና የራሳቸውን የቴክኖሎጂ አቅም እንዲገነቡ የሚያግዝ 3 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዓለም አቀፍ ፈንድ እንዲቋቋም ጥሪ አቅርቧል።
የተባበሩት መንግሥታትዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እንደገለጹት፤ የኤአይ ቴክኖሎጂ እጅግ ፈጣን እድገት በጥቂት አገራት ብቻ ተወስኖ መቅረት የለበትም። በመሆኑም በታዳጊ አገራት የሚስተዋሉ የቴክኖሎጂና የአቅም ክፍተቶችን ለመሙላት የተቀናጀ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ማድረግ አስገዳጅ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ለዚህ ዓላማምሥራ ይጀምራል ተብሎ በሚጠበቀው የመጀመሪያዎቹ ከ2 እስከ 4 ዓመታት ውስጥ 3 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ለመሰብሰብ ታቅዷል። የተሰበሰበው ገንዘብ በታዳጊ አገራት የኤአይ መሠረተ ልማትን ለማጠናከር፣ የሰው ኃይልን ለማሰልጠን እንዲሁምየዲጂታልና ተቋማዊ አቅምን ለመገንባት የሚያገለግል ይሆናል።
የፈንዱ የመጨረሻግብ የቴክኖሎጂ ልማት በጥቂት የበለጸጉ ሀገራት ብቻ እንዳይወሰን ማድረግ ሲሆን፤ ይህም ታዳጊ ሀገራት የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚደረገው የወደፊት የኤአይ ዕድገት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያስችል ወሳኝ ዕድል ይፈጥራል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute