የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከቼቼ ቴክኖሎጂስ ጋር የትብብር ስምምነት አደረገ።
· MOU
The partnership aims to enhance technology development, human resource capacity building, and private-sector collaboration to support Ethiopia’s digital transformation and address national challenges through innovation.
ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በቴክኖሎጂ ልማት፣ በሰዉ ኃይል እና በሌሎች የቴክኖሎጂ አስቻይ ልማቶች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ያለመ ነዉ። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ወቅት በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ የግል ቴክኖሎጂ ተቋማትን ለማገዝ በኢንስቲትዩቱ በኩል በትብብር ለመስራት ዝግጁነት መኖሩን አስረድተዋል። በመሆኑም በቀጣይ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በሚያደርጉት የስራ ትብብር የሃገራችንን ችግሮች በቴክኖሎጂ ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰሩ አስገንዝበዋል።
የቼቼ ቴክኖሎጂስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሬድዋን አማን በበኩላቸዉ ተቋማቸዉ በኢትዮጵያ የዲጂታል ጉዞ ላይ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል። ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል እድል በማግኘታቸዉም ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
ቼቼ ቴክኖሎጂስ በተለያዩ ዓለማቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት ዉስጥ ሲሰሩ የነበሩ ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን የመሰረቱት የግል ቴክኖሎጂ ተቋም ነዉ።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute