“እያንዳንዱ ሀገር የራሱ የሆነ ኤ.አይ የሚመራበት ስትራቴጂ ያስፈልገዋል”- ሳም አልትማን
· Other
OpenAI CEO Sam Altman Urges Nations to Develop Independent AI Strategies and Ensure Global Accessibility at GITEX GLOBAL 2025.
የኦፕን ኤ.አይ (OpenAI) ኩባንያ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆነው ሳም አልትማን በዱባይ በሚካሄደው ጂ.አይ.ቴክስ ግሎባል (GITEX GLOBAL) የቴክኖሎጂ ጉባኤ ላይ "እያንዳንዱ ሀገር የራሱ የሆነ ኤ.አይ የሚመራበት ስትራቴጂ ያስፈልገዋል" በማለት አሳስቧል።
ሀሳቡን በበይነመረብ አማካኝነት ያስተላለፈው ሳም አልትማን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በዓለማቀፍ ደረጃ በስፋት ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ተናግሯል።
ገልፍ ኒውስ በድረገጹ እንዳስነበበው የኤ.አይ ቴክኖሎጂን ተደራሽ ማድረግ፣ ለዜጎች አጠቃቀሙን ማስተማር እና ርካሽ በማድረግ የቴክኖሎጂ ክፍፍልን ለማስቀረት መሰራት እንዳለበት ሳም አልትማን በንግግሩ አጽንኦት ሰጥቷል።
ከዚህ በተጨማሪም ለኤ.አይ ቴክኖሎጂ እድገት የኃይል አቅርቦት እና የዳታ ማዕከላት ዋነኛው ገደብ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁሟል። ለዚህም ሀገራት አጋርነትን መፍጠር እና የተቀናጁ ስትራቴጂዎችን መንደፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግሯል።
“Powering the Future through AI & Tech” በሚል መሪ ቃል በዱባይ እየተካሄደ በሚገኘው የጂ.አይ.ቴክስ ግሎባል (GITEX GLOBAL) ሁነት ላይ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑካን ቡድን እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute