ጃፓን በኢትዮጵያና በአፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍን ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነት ገለጸች፡፡
· Visiting
Hashimoto Yasuhiro of Ministry of Economy, Trade and Industry visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to strengthen collaboration in AI innovation and support startup development.
የጃፓን የኢኮኖሚ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር (METI) የአፍሪካ ዋና ተወካይ ሀሺሞቶ ያሱሂሮ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ሀሺሞቶ ያሱሂሮን እና ልዑካቸውን ተቀብለው ኢንስቲትዩቱ ስለሚሰራቸው ስራዎች ገለፃ አድርገዋል። በገለፃቸውም ኢንስቲትዩቱ የማህበረሰብን ችግሮች ለመፍታት ከሚሰራው ስራ በተጨማሪ ስታርታፖችን በመደገፍ እያከናወነ ስላላው ተግባራትና በዩኒፖድ በኩል እተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የጃፓን የኢኮኖሚ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአፍሪካ ዋና ተወካይ ሀሺሞቶ ያሱሂሮ በኢንስቲትዩቱ ውስጥ የሚገኙ ስታርታፖች ያላቸውን አቅምና ተነሳሽነት አድንቀዋል፡፡ ስታርታፖቹን ከዓለማቀፍ የቴክኖሎጂ ሥነ-ምህዳር ጋር ለማገናኘት በሚቀጥሉት ዓመታት ወጣቶችን በዘርፉ ለማብቃትና ለመደገፍ የሚያስችል ስራ በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
ተወካዩ ጃፓን የኤ.አይ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋትና ለመደገፍ በትኩረት እንደምትሰራ ገልፀው፤ ወጣቶች ያላቸውን የኤ.አይ እውቀት ወደ ምርት እና አገልግሎት እንዲቀይሩት ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።
የጃፓን መንግስት በአህጉሪቱ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በቴክኖሎጂ ለመፍታትና የአካባቢውን የፈጠራ ስራዎች ለመደገፍ ሙሉ ቁርጠኝነት እንዳለው በዚሁ ወቅት ተመላክቷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute