ለጉዞ ጥያቄዎች፣ ፍለጋ እና ቦታ ለማስያዝ የሚያገለግል የኤ.አይ ሞዴል ይፋ ሆነ፡፡
· AI Solutions
Kayak Launches AI Mode Powered by ChatGPT to Revolutionize Travel Planning with Smarter, Personalized, and Voice-Enabled Trip Assistance.
የጉዞ መፈለጊያ አውታር የሆነው ካያክ (Kayak) ተጠቃሚዎች ወደ ጉዞ መዳረሻቸው ከመሄዳቸው በፊት ስለ ጉዟቸው ምርምር እንዲያደርጉ የሚያስችል የኤ.አይ ሞዴል ይፋ አደረገ።
ይህ ስርዓት ተጠቃሚዎች የጉዞ ነክ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ እንዲሁም በድርጅቱ ድረ-ገጽ ላይ ከተቀናጀው የኤ.አይ ቻትቦት ጋር በመነጋገር በረራዎችን፣ ሆቴሎችንና መኪናዎችን እንዲያወዳድሩና ቀድመው እንዲያስይዙ ያስችላቸዋል።
ይህ ሞዴል የጉዞ ሀሳቦችን፣ የዋጋ ቅናሾችን፣ ንጽጽር እና የዋጋ ትንበያን የመሰሉ የተጠቃሚዎች ጥያቄን መመለስ የሚችል ነው፡፡ ሰዎች የጉዞ ዕቅድ ሲያወጡ ከጊዜ እና ከወጭ አንፃር ተስማሚ የሆኑ አማራጮችን በማቅረብም ያግዛል።
ይህ ሞዴል በሞባይል እና በድረ-ገጽ አማራጭ የቀረበ ሲሆን አውዳዊ ትርጉምን የያዙ ውጤቶችን ለመስጠት ከቻት ጂ.ፒ.ቲ ጋር ያለውን ውህደት ይጠቀማል ተብሏል።
ሞዴሉ ለጊዜው በእንግሊዝኛ ቋንቋ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ብቻ የቀረበ ሲሆን፤ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ወደ ሌሎች አገሮች እና ቋንቋዎች ለማስፋፋት ማቀዱን ኩባንያው አሳውቋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute