የኤአይ አዲስ ምዕራፍ፡ ትኩረቱ በውጤታማነት እና ዘላቂ አጠቃቀም ላይ
· AI Solutions
As global AI spending accelerates, cost efficiency, infrastructure, governance and sustainable deployment are becoming as important as model performance, creating new opportunities for emerging digital economies such as Ethiopia.
የዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ገበያ ትኩረት ከቀላል የ ኤአይ ሞዴሎችሙከራ ወደ ወጪ ቆጣቢነት፣ መሠረተ ልማት እና ዘላቂ አጠቃቀም እየተሸጋገረ መምጣቱን የ TechRadar Pro ጥናት አመላክቷል።
ጥናቱ እንዳመላከተው በፈረንጆቹ 2026 የዓለም አቀፍ የ ኤአይ ኢንቨስትመንት 44 በመቶ በመጨመር 2.52 ትሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፤ ከዚህ ውስጥም 1.37 ትሊዮን ዶላር የሚሆነው ለ ሰው ሰራሽ አስተውሎት መሠረተ ልማት ብቻ የሚመደብ ነው።
የኢንዱስትሪው የመጀመሪያው ምዕራፍ በዋነኝነት ያተኮረው በአፈጻጸማቸው የላቁ ሞዴሎችን በማበልጸግ እና መተግበር ላይ ነበር። አሁን ግን ድርጅቶች ወደ "AI 2.0" ምዕራፍበመሸጋገር የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ታሳቢ ያደረገ፣ ፍጥነትን እናደህንነትን ባረጋገጠአሠራር ላይ ትኩረት ማድረግ ጀምረዋል። የቶከኖች ዋጋ በየዓመቱ ቅናሽ እያሳየ ነው፡፡ በዚህም ኩባንያዎችኤአይንበስፋት በበርካታ የሥራ ዘርፎች ላይ እየተጠቀሙበት ነው፡፡
በሌላ በኩል በተለይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተከታታይ ውስብስብ ሥራዎችን በራሱ እንዲሠራ የሚያስችለው “ኤጀንቲክ ኤአይ” (Agentic AI) አጠቃቀም እየጨመረመምጣቱ ደግሞ ለኮምፒውተር ግብዓት ያለውን ፍላጎት ከፍ አድርጎታል። ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ ይህ ለውጥ እንደ ኡበር ያሉ ትላልቅ ኩባንያዎች የ ኤአይ ኢንቨስትመንታቸውን እንዲያሳድጉ እና የቴክኖሎጂውን አቅም በስራዎቻቸው ላይ እንዲተገብሩ አስችሏል።እንደ ዲካጎን ያሉ ተቋማት ደግሞ ክፍትምንጭ አሰራሮችን በመጠቀም ወጪያቸውን በስድስት እጥፍ መቀነስ ችለዋል።
ይህ የገበያ ለውጥ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሀገራት ትልቅ ዕድል ይፈጥራል። ሀገራት እጅግ ውድ የሆኑ መሠረታዊ ሞዴሎችን ከዜሮ ጀምሮ ለመገንባት ግዙፍ ወጪ ከማውጣት ይልቅ በአዋጭ የኤአይ አጠቃቀም፣ምቹ መሠረተ ልማት፣የአገር ውስጥ የውሂብ አቅም እና ሀገራዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መፍታት ላይ ማተኮር እንደሚችሉ የዘርፉ ተንታኞች ያስረዳሉ።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute