የተቀናጀ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ሥርዓት ይፋ ሆነ።
· AI Solutions
Addis Ababa Launches New CRVS e-ID System to Advance Digital Public Services
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አልምቶ የሰጠዉ የተቀናጀ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ሥርዓት (CRVS e-ID Integrated System) በዛሬዉ ዕለት በይፋ ተመርቋል።
ሥርዓቱ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የሚሰጣቸዉን ሁሉንም አይነት አገልግሎቶች በበይነ መረብ እንዲሁም በሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት ማግኘት ያስችላል። ይህም ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው ጉዳያቸዉን በቀላል ማስፈጸም እንዲችሉ አጋዥ ነዉ።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ለምርቃት የበቃው ሲስተም ስርአት ብቻ ሳይሆን ብሄራዊ ሀብት ነው ብለዋል። ሥርዓቱ ኢንስቲትዩቱ ሀገርን ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማድረግ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ መሆኑንም ገልፀዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ይህ ሥርዓት እውን እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸዉ ሥርዓቱ ኢንስቲትዩቱ የደረሱበትን አቅም ያሳየ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል። ሥርዓቱ ኤጀንሲዉን ይበልጥ ተደራሽ፣ዉጤታማ እንዲሁም ከብልሹ አሰራር የጸዳ ለማድረግ አስቻይ ነዉ ብለዋል።
ቴክኖሎጂዉን ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸዉና በቅርቡ በተመረጡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 50 ወረዳዎች አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር በመድረኩ ተገልጿል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute