የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡
· Visiting
Indian External Affairs Minister Visits EAII to Advance Ethiopia–India Cooperation in Artificial Intelligence, Innovation, and Digital Transformation
የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር (ዶ/ር) እና ልዑካቸው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለንስ ኢንስቲትዩትን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ለልዑካን ቡድኑ ባደረጉት ገለጻ፣ ተቋሙ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ የፈጠራ ሥራዎችን በማበልጸግ በሀገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ እያበረከተ ያለውን ስትራቴጂካዊ ተግባራት አብራርተዋል። ኢንስቲትዩቱ በጤና፣ በግብርና እና በዲጂታል መሠረተ ልማት ዘርፎች እያመጣ ያለውን ተጨባጭ ለውጥም ለልዑካኑ አስረድተዋል።
የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር (ዶ/ር) በኢንስቲትዩት የሚሰሩ የቴክኖሎጂ ስራዎችን አድንቀዉ ሀገሪቱ ለኤ.አይ ቲክኖሎጂ በዚህ ደረጃ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑ ከቴክኖሎጂው ዘርፍ ተጠቃሚ ለመሆን ያላትን ቁርጠኛ አቋም ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute