የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ላይ ያላትን ራዕይ እና ተጨባጭ እርምጃዎችን አደነቀ
· Other
The World Bank has recognized Ethiopia’s growing artificial intelligence ambitions, encouraging the country to strengthen digital infrastructure, skills, data systems, and local AI adoption as foundations for long-term technological innovation.
ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን የሀገራዊ ልማት አስኳል ለማድረግ ያላት ጠንካራ ፍላጎት ከዓለም ባንክ ገንቢ ትኩረት አግኝቷል። ባንኩ ሀገሪቱ የቴክኖሎጂ
ፈጠራዎችን ከማጎልበት ጎን ለጎን የቴክኖሎጂ መሠረቶቿንም እንድታጠናክር አበረታቷል።
iAfrica ድረ-ገጽ በዘገባው የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ጉዞ ውስጥ ትልቅ አቅም እየተፈጠረ መሆኑን ስለመመልከቱ ገልጿል። እንዲሁም ነባር ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎችን በመቀበልና ከሁኔታዎች ጋር በማስማማት ለላቀ ፈጠራ የሚያስፈልጉ አቅሞችን በመገንባት ላይ ቅድሚያ የሚሰጥ አካሄድ እንደሚመከር ባንኩ አመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይ፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የዲጂታል ክህሎት ልማት እና የ5 ሚሊዮን ኮደሮች መርሃ ግብርን ጨምሮ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት ወሳኝ እርምጃዎችን ወስዳለች።
የዓለም ባንክ አቋም የዲጂታል መሠረተ ልማትን ማስፋፋት፣ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሃይል ማልማት፣ የውሂብ (ዳታ) ሥነ-ምህዳሮችን ማጠናከር እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን እንደ ግብርና፣ ጤና ጥበቃ፣ ትምህርት፣ የህዝብ አገልግሎቶች እና በሌሎችም ሀገራዊ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች ላይ ተግባራዊ የማድረግን አስፈላጊነት ይደግፋል።
ይህ ምክረ ሃሳብ ከኢትዮጵያን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ራዕይ የሚስማማ እና ሀገሪቱ ነባር ቴክኖሎጂዎችን ከመቀበል ጀምሮ ለአካባቢያዊ ፍላጎቶች ከማስማማት
ባለፈ ሀገረኛ መፍትሄዎች እስከማበልጸግ ያለውን ሂደት ያሳያል። ተግባራዊ እየሆነ ባለው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዋ እና እያደገ በመጣው የአርቲፊሻል
ኢንተለጀንስ አቅም አማካኝነት ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂን የልማት ስትራቴጂዋ ዋና አካል አድርጋለች፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute