በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለሚገኙ የመንግሥት ሰራተኞች እና የአይ.ሲ.ቲ ባለሞያዎች የኤ.አይ ክህሎት ማበልፀጊያ ስልጠና መስጠት ተጀመረ።
· Education
EAII and Partners Launch “AI for Government” Training in Sidama to Advance Digital Public Services
ስልጠናው በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በዩ.ኤን.ዲ.ፒ ትብብር የተዘጋጀ ነው።
የስልጠና መድረኩን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ በንግግር ከፍተዋል። በንግግራቸው ስልጠናው በዚህ ዓመት ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ቀጥሎ በሐዋሳ ከተማ እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ከግብ ለማድረስ ስልጠናው አጋዥ መሆኑን በመግለጽ፤ የቴክኖሎጂውን ግንዛቤ ማካበት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። ቴክኖሎጂ የመወዳደሪያ ሜዳ እየሆነ ባለበት በዚህ ዘመን የመንግሥት አገልግሎትን በቴክኖሎጂ መደገፍ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው መሆኑንም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የስራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ ኢንስቲትዩቱ ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ እየሰራ የሚገኘውን ስራ አድንቀዋል። በክልሉ የመንግሥት አገልግሎት ሪፎርሞች እየተሰሩ ባሉበት በዚህ ወቅት የሚሰጠው ይህ ስልጠና ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ኃላፊዋ ገልፀዋል።
‘’Ai for Government’’ በሚል ርዕስ የሚሰጠው ስልጠናው ለመንግሥት ሰራተኞች መሰረታዊ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ግንዛቤን ከማስጨበጥ ጀምሮ ለስራቸው አጋዥ የሆኑ የኤ.አይ ክህሎቶች የሚዳሰሱበት ይሆናል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute