የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራርና ሰራተኞች የነጭ ሪባን ቀንን አከበሩ፡፡
· Other
EAII Observes White Ribbon Day, Highlighting AI’s Role in Advancing Women’s Safety and Empowerment
‘’ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ‘’ በሚል መሪ ቃል በዓለማቀፍ ደረጃ ለ34ተኛ ጊዜ የሚከበረውን የነጭ ሪባን ቀን በንግግር የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ቶሎሳ ኢንስቲትዩቱ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በመርሓ ግብሩ ላይ በጋዜጠኛ ማርታ ደጀኔ በዲጅታል መንገድ ስለሚፈጸም የሴቶች ጥቃት የተመለከተ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን በኢንስቲትዩቱ የተዘጋጀ ኤ.አይ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለዉን ሚና የተመለከተ ጥናት ቀርቧል፡፡
በተጨማሪም ኢንስቲትዩቱ የጡት ካንሰርን ለመመርመር የሚያግዝ ሲስተም እንዲሁም ሌሎች የጾታ እኩልነት የሚያረጋግጡ ስርአቶችን በማበልፀግ የሴቶችንና እናቶችን ጤናና ደህንነት ለመጠበቅ እየሰራ እንደሚገኝ ተብራርቷል፡፡
በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች መብት ስርጸት ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ ማህሌት አማረ በሃገርአቀፍ ደረጃ የሴቶችን ጥቃት ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አብራርተዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute