የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በቴክኖሎጂ ትብብር ዙሪያ መከሩ
· Visiting
A delegation from the Ethiopian Capital Market Authority visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to explore how artificial intelligence can improve capital market operations, while discussing cooperation in technology, human resource development, and knowledge transfer.
በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ራሄል ካሳ የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝቷል። የኢንስቲትዩቱየዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ እና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች አማካሪ ሻምበል ይልማ (ዶ/ር) የኢንስቲትዩቱን የስራ እንቅስቃሴ አስጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ራሄል ካሳ ጉብኝቱ ብዙ ነገሮችን ያየንበት፤ ኢንስቲትዩቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ስራዎች መስራቱን የተገነዘብንበት ነው ሲሉ ገልጸዋል። በተለይም የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ያሰራር ሂደቶችን በኤ.አይ የታገዙና ዉጤታማ ከማድረግ አንጻር በጋራ መስራት የሚቻልባቸዉ መስኮችን መለየት መቻላቸዉን አስታዉቀዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከቴክኖሎጂ ልማት እንዲሁም የህዝብ ግንኙነት አንጻር የሚያከናውናቸውን ተግባራት በተመለከተ ልምዱን
ለልዑካኑ አካፍሏል።ሁለቱ ተቋማት በሰው ሀይል ልማት፣በቴክኖሎጂ እንዲሁም በዕውቀት ሽግግር ዙሪያ በጋራ መስራት የሚችሉባቸውን ጉዳዮች አስመልክቶ ሰፋያለ ውይይት ተደርጓል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute