ኢንስቲትዩቱ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ዙሪያ እየሰራ ያለው ተግባር እንደ ሞዴል ሊወሰድ የሚችል መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ አመራሮች ገለፁ፡፡
· Visiting
Zambian Defence Delegation Commends Ethiopia’s Progress in AI and National Innovation
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ አመራር እና ዳኞች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መሥሪያ ቤት የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ለጎብኚዎቹ አጠቃላይ የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ ኢንስቲትዩቱ የተቋማችን አጋር ሆኖ አብረን ስንሰራ የቆየነውን ተግባር ከፍ ለማድረግ ያስቻለ ጉብኝት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ኢንስቲትዩቱ በፍትሕ ዘርፍ እያደረገ ያለው አስተዋፆ ታላቅ ነው ያሉት ም/ፕሬዝዳንቷ እንደ ሀገር አሉን ከምንላቸው እና ከምንኮራባቸው ተቋማት አንዱ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መሆንኑን ጠቁመዋል፡፡
በጠቅላይ ፍርድ ቤት የምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ዳኛ አበበ ሰለሞን በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ በኤ.አይ ዘርፍ እየሰራ ያለው ተግባር እንደ ሞዴል ሊወሰድ የሚችል መሆኑን በምልከታቸው ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል፡፡
ጉብኝቱ በጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በኢንስቲትዩቱ በጋራ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የማስፋት እና በተግባር አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የስማርት ኮርት ስርዓት ለማዳበር የሚያስችል ነው፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute