የመገናኛ ብዙኃን አቅምን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እና የሕግ ማስፈጸም ሥራን ለማጠናከር የሚያስችል የተቋማት ስምምነት ተፈረመ::
· MOU
Eleven government institutions, including the Ethiopian Artificial Intelligence Institute, signed a Memorandum of Understanding to strengthen media regulation through artificial intelligence, cybersecurity awareness, data exchange, coordinated oversight, and institutional capacity building.
የኢትዮጵያአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ አስራ አንድ የመንግስት ተቋማትን ያካተተ ውጤታማ የሚዲያ ሬጉላቶሪ ስርዓትን ማጠናከር አላማው ያደረገ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የፊርማ ስነ-ስርዓት ተካሄዷል።
የመገናኛ ብዙኃን ቁጥጥርና የአቅም ግንባታ ስራዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በማስተሳሰር ቅንጅታዊ አሠራር ለመዘርጋት የተዘጋጀው የመግባቢያ ሰነድ፤ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ እና የዋናዳይሬክተሩ የቴክኖሎጂ አማካሪ ሻምበል ይልማ (ዶ/ር) ጨምሮ የየተቋማቱ ኃላፊዎች ፈርመዋል።
በተቋማቱ መካከል የተደረገው የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ የሚዲያ ሬጉሌሽን አጋዥ የሆኑ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስርዓቶችን ለማልማት፣ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ለመፍጠር፣ የመረጃ ትስስርና ልውውጥ ለማድረግ፣ የቁጥጥር ስርዓት በተደራጀ መንገድ ለመምራት እና ክትትልና አቅም ግንባታን ለማጎልበት እንዲሁም የሕግ የበላይነትን ለማስፈን የሚያስችል ነው።
የስምምነቱን አስፈላጊነት በተመለከተ እና መጥራት ያለባቸው የተቋማቱ የግንኙነት መስመሮችን መለየት ያስቻለ ውይይት በመድረኩ ተሳታፊዎች ተካሄዷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute