የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመራሮች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩቱን ጎበኙ።
· Visiting
National Intelligence and Security Service Delegation Explores EAII’s AI Solutions for National Development.
ኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የኢንስቲትዩቱን የስራ እንቅስቃሴ ለአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ አመራሮች ገለጻ አድርገዋል።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ርስቱ ይርዳው የኢንስቲትዩቱ የምርምር እና ልማት ስራ የሀገር ችግር የሚፈታ እና የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ መሆኑን ከጉብኝቱ መገንዘባቸውን ገልፀዋል። አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ከቴክኖሎጂ ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ከኢንስቲትዩቱ ልምዶች በመዉሰድ በጋራ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በጉብኝቱ የኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ዲጂታል ቤተ መጽሐፍት፣የሮቦቲክስ ወርክሾፕ እንዲሁም የምርት ማሳያ ክፍሎች ምልከታ ተደርጎባቸዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute