የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና አርሲ ዩንቨርሲቲ በምርምር እና ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራ ተወያዩ፡፡
· Visiting
A delegation from Arsi University visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to observe its technology projects and discuss future collaboration in research, particularly in agriculture and healthcare.
የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን በመጎብኘት የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴዎችና የቴክኖሎጂ ስራዎች ተመልክቷል።
በጉብኝቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ ኢንስቲትዩቱ ስላከናወናቸው አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።ከጉብኝቱ ጎን ለጎንም ሁለቱ ተቋማት ወደፊት ሊኖራቸው ስለሚችለው የትብብር ግንኙነት ውይይት አካሂደዋል።
የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት ረዳት ፕሮፈሰር የሆኑት ሀጫሉ አቶምሳ (ዶ/ር) የኢንስቲትዩቱስራዎችና የቴክኖሎጂ እድገት የኢትዮጵያን ብሩህ ተስፋ የሚያሳዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። አያይዘውም ተቋማቱ በቀጣይ በግብርና እና በጤና ዘርፍ በሚደረጉ ምርምሮች በጋራ በመስራት
ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ተናግረዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute