ሶስት የፌደራል ተቋማት በ19 ሚሊዮን ብር ወጪ በጋራ ለሚገነቧቸው ትምህርት ቤቶች በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
· Other
The Ethiopian Artificial Intelligence Institute, Information Network Security Administration and Federal Civil Service Commission have jointly launched the construction of two pre-primary schools in East Hararghe Zone, while providing educational materials to 720 students.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የፌዴራል ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በጋራ በመሆን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ባሉ ሁለት ወረዳዎች ላይ የትምህርት ቤቶች ግንባታ የተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች አስጀምረዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ በግንባታ ማስጀመሪያ መርሓግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ሶስቱ ተቋማት በጋራ በመሆን ከከተሞች እርቀው በሚገኙ ወረዳዎች ላይ የሚገነቡት ትምህርት ቤት በአካባቢው የሚገኙ ታዳጊዎች በአቅራቢያቸው የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ያደርጋል ብለዋል።
የምስራቅ ሀረርጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መሐመዲን ከቢርሁሴን በበኩላቸው ተቋማቱ ለዞኑ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋ አቅርበው የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ በርካታ ታዳጊያዎች በትምህርት ገበታቸው እንዲገኙ ያስችላል ብለዋል።
በ19 ሚሊዮን ብር ወጭ የሚገነቡት ሁለት ቅድመ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታቸው ለአካባቢው ሞዴል በሆነ መንገድ በከፍተኛ ጥራት ተገንብተው ከአንድ ወር ያነሰ ጊዜ ተጠናቆ ለመጭው የትምህርት ዘመን ዝግጁ ይሆናሉ ተብሏል።
ከትምህርት ቤቶች ግንባታ በተጓዳኝ በዞኑ ስር ባሉ ሶስት ወረዳዎች ለሚማሩ 720 ታዳጊዎች የሚሆን የትምህርት መሳሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ በተቋማቱ ተደርጓል፤
ድጋፉንም የተቋማቱ ኃላፊዎች በወረዳዎቹ በመገኘት አስረክበዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute