ካናዳ በኤአይ አዲስ የሰብል ዝርያዎችን የማልማት ምርምርን እየደገፈች ነው
· AI Study
Canada Invests in AI-Powered Crop Research to Develop Climate-Resilient, High-Yield Varieties
የካናዳ መንግሥት በሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት በሽታና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙእና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን
ለማልማት 600 ሺህ ገደማ የካናዳ ዶላር ድጋፍ አድርጋለች።
የካናዳ ግብርናና ግብርና ነክ ምርቶች ሚኒስቴር የድጋፉ ዓላማ የአኩሪ አተርና የገብስ ዝርያዎችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በመታገዝ በአጭር ጊዜ ማልማት ነው ብሏል።
በተለምዶ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን ከምርምር ጀምሮ ለገበያ እስኪቀርቡ ድረስ ከ10 ዓመታት በላይ ሊወስድ እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን፤ አዲሱ ቴክኖሎጂ ይህንን ሂደት ያሳጥረዋል፡፡
የካናዳ መንግሥት እንደገለጸው በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሚታገዙ የግብርና ምርምሮች የሰብል ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ አርሶ አደሮች የአየር ንብረት
ለውጥን እንዲቋቋሙ፣ የምግብ ዋስትናን እንዲያረጋግጡና የግብርና ዘርፉን ተወዳዳሪነት እንዲያጠናክሩ ያግዛሉ።
ኢትዮጵያም የግብርና ዘርፏን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለማዘመን እየሰራች ነው፡፡ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የለሙት እንደ ቡና፣ስንዴ፣
እንሰት እና ቲማቲም ባሉ ሰብሎች የበሽታ ልየታ እና ምርታማነትን የሚያሳድጉ የኤአይ መፍትሔዎች ለዚህ ተጠቃሽ ነው፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute