የአባይ ባንክ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የስራ ጉብኝት አካሄዱ።
· Visiting
Abay Bank Officials Visit EAII to Strengthen Collaboration for Economic Growth and Productivity Enhancement.
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ለኃላፊዎቹ ማብራሪያ አቅርበዋል። ኤ.አይ ለሁሉም በሚለው የኢንስቲትዩቱ መሪ ቃል መሰረት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹ ሲሆን፤ ከባንኩ ጋርም በጋራ ለመስራት ኢንስቲትዩቱ ዝግጁ መሆኑን አመላክተዋል።
የአባይ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የኋላ ገሠሠ በበኩላቸዉ የባንኩ ዘርፍ ከቴክኖሎጂ ጋር ሰፊ ቁርኝት ያለዉ እንደመሆኑ በጋራ መስራት መልካም አጋጣሚ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም ኢንስቲትዩቱ በስታርታፖች ዙሪያ እያከናወነ ያለዉ ስራ ለሀገር ጠቃሚ የሆነ ተግባር መሆኑን በማንሳት ባንኩ አስፈላጊዉን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታዉቀዋል። ኢንስቲትዩቱ ሀሳብ ወደ ተግባር በአጭር ጊዜ ወደ መሬት ወርዶ የታየበት መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚዉ በንግግራቸዉ አክለዋል።
በቀጣይም በአቅም ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ድጋፍ እና መሰረተ ልማቶችን በጋራ ከመጠቀም አኳያ በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ ዉይይት ተደርጓል።
የባንኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በኢንስቲትዩቱ የሚገኘዉን የኤ.አይ ስታርታፕ ማዕከል፣ የሮቦቲክስ ወርክ ሾፕ እና የምርት ማሳያ ክፍሎችን በጉብኝታቸዉ ተመልክተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute