“የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዘርፍ አቅም ለሀገሪቱ ዘላቂ ዕድገት ጠንካራ መሠረት ነው” የአሜሪካ ኤምባሲ ከፍተኛ ልዑክ
· Visiting
U.S. Embassy Delegation Visits EAII to Explore Expanded AI and Technology Cooperation
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከሀገራትና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ያለውን የቴክኖሎጂ ትብብር በማጠናከር ላይ ነው በዚሁ ጥረት የአሜሪካ ኤምባሲ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ኢንስቲትዩቱንጎብኝቷል።
በጉብኝቱ ወቅትየኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬግርማ(ዶ/ር) እንግዶቹን ተቀብለው ኢንስቲትዩቱ በሮቦቲክስ፣ በስማርት ፖሊስ ስቴሽን፣ በካርጎ
ትራኪንግና በሌሎች ዘርፎች ያስመዘገባቸውን ውጤቶች አስጎብኝተዋል።
አሁን በመካሄድ ላይ ያሉ አዳዲስ የምርምርና ልማትሥራዎችንም በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በውይይቱ ላይየአሜሪካ ተቋማት በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዘርፍ በመሳተፍ አጋርነታቸውን የሚያሳዩባቸውሰፊ ዕድሎች እንዳለ ተነስቷል።
ከልዑካን ቡድኑአባላት መካከል የምስራቅ አፍሪካ የውጭድጋፍ ማዕከል ምክትል አስተባባሪ ሶሌዳድ ሮጀርስ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊትበመለየትና ፈጣንመፍትሄ በማበጀት ረገድ ያለውን ወሳኝሚና አንስተዋል። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዓለምእያደረገች ያለውጉዞ ለሀገሪቱ ዕድገት ትልቅ ምዕራፍ መሆኑንም ገልጸዋል። አክለውም የኢትዮጵያና የአሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነት በቴክኖሎጂው ዘርፍም በጠንካራ መሠረት ላይ መቀጠሉን ተናግረዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute