“ኤ.አይ ዩኒፖድ የትብብር ውጤት ማሳያ ነው፡፡” የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
· Education
Deputy Prime Minister Temesgen Tiruneh inaugurates AI UniPod Innovation Center to advance African-led technology and data sovereignty.
በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ትብብር በቲምቡክቱ ኢንሼቲቭ አማካኝነት የተገነባው የኤ.አይ ዩኒፖድ የፈጠራ ማዕከል የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠ/ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በክብር እንግድነት በተገኙበት በይፋ ተመርቋል፡፡
በምረቃ መርሓ ግብሩ ላይ ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ኤ.አይ ዩኒፖድ በጠንካራ ተቋማት ትብብር የተመሰረተ የፈጠራ እና የቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ማዕከል መሆኑን አንስተዋል፡፡ ማዕከሉ ሀሳቦች ወደ ተግባር የሚቀየሩብት በአፍሪካውያን፤ ለአፍሪካውያን የሚያገለግል ይሆናል ብለዋል፡፡
ባለንበት ዘመን የሀገራት ሉዓላዊነት ትርጓሜ ከድንበር በዘለለ በዳታ ባለቤትነት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ከቴክኖሎጂው ልማት ባሻገር የዳታ ሉዓላዊነት ትኩረት እንደሚሻ ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
ማዕከሉ የተሟላ የመስሪያ ቦታ እና የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትን በጋራ አጣምሮ የያዘ ሲሆን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ ስታርታፖች እና ስራ ፈጣሪዎች የሚደገፉበት ምቹ የመመራመሪያ እና የፈጠራ ሥፍራ ነው፡፡
በምርቃት መርሓ ግብሩ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የዩኤንዲፒ የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute