አንድ ኳድሪሊዩን ስሌቶችን በአንድ ጊዜ ማስላት የሚያስችለው ሱፐር ኮምፒዩተር ተዋወቀ።
· AI Solutions
NVIDIA Unveils DGX Spark — the World’s Smallest AI Supercomputer Designed to Democratize Supercomputing Power for Developers and Innovators.
ኢንቪዲያ በዓለም ላይ ትንሹ የሆነውን ኤ.አይ ሱፐር ኮምፒዩተር ዲ.ጂ.ኤክስ ስፓርክን (DGX Spark) አስተዋውቋል።
ዲ.ጂ.ኤክስ ስፓርክ (DGX Spark) በኤ.አይ ዘርፍ ለተሰማሩ ተመራማሪዎች፣ ተማሪዎች እንዲሁም የቴክኖሎጂዉ አበልጻጊዎች ምቹ መሆኑ ተነግሯል። ሱፐር ኮምፒዩተሩ ተጠቃሚዎች ያለምንም ተጨማሪ ወጪ ዳታዎችን ፕሮሰስ ማድረግ እንዲሁም ሞዴል ማስተማር እንዲችሉ አስቻይ ነዉ።
በተጨማሪም ከተለያዩ የኢንቪዲያ ኩባንያ ምርቶች ጋር አቀናጅቶ መጠቀም የሚያስችል አማራጭ አለዉ። የኩባንያዉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጄንሰን ሁዋንግ ዲ.ጂ.ኤክስ ስፓርክ ዋና አላማ የኤ.አይ አበልጻጊዎች ሱፐር ኮምፒዩተሮችን እንዲያገኙ ማስቻል ነዉ ብለዋል።
ዲ.ጂ.ኤክስ ስፓርክ የኤ.አይ ኤጀንቶችን፣ ቻት ቦቶችን እና የተለያዩ የኤ.አይ ስርዓቶችን ለማበልጸግ ያግዛል።
ለዚህም እንዲረዳ 1ፔታ ፍሎፕ የፕሮሰሲንግ (አንድ ኳድሪሊየን ስሌቶችን በአንድ ጊዜ የማስላት) አቅም ተላብሷል። ኢንቪዲያ ሱፐር ኮምፒዩተሩን ለማበልጸግ ከአሰስ እና ዴል የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር በጋራ መስራቱን ገልጿል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute