የቡና ባንክ የስራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የስራ ጉብኝት አካሄዱ፡፡
· Visiting
Bunna Bank Executives Visit EAII to Explore AI Partnership for Financial Growth, Data Innovation, and Productivity
በቡና ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ የተመራዉ ልዑክ በኢንስቲትዩቱ በመገኘት ቀጣይ አጋርነት ለመፍጠር ያለመ ጉብኝት አካሂዷል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ኢንስቲትዩቱ በፋይናንስ፣ በጤና፣ በግብርና፣ በአገልግሎት እና ሌሎችም ዘርፎች ያከናወናቸውን ስራዎች አብራርተዋል፡፡ በዚህም ተግባራዊ ለውጦች መመዝገባቸውን ለልዑካኑ ገልጸዋል፡፡
የቡና ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሙሉጌታ አለማየሁ በበኩላቸው “ጉብኝቱ ብዙ የተማርንበት እና ኤ.አይን በተመለከተ በሩቅ ስንሰማ የነበረውን በቅርበት ለማየት
የቻልንበት ነው፡፡” ሲሉ ገልጸዋል፡፡የዳታን ዓለማቀፋዊ አስፈላጊነት ያብራሩት ዋና ስራ አስፈጻሚው በዚህ ረገድ ኢንስቲትዩቱ ካከናወናቸው ተግባራት ባንካቸው ብዙ ትምህርት እንደሚወስድ ጠቁመዋል፡፡
በጉብኝቱ ባንክን ጨምሮ የትኛውም አይነት ስራ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ላይ መመርኮዝ ካልቻለ ተወዳዳሪነቱ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ እንደሚሆን ተመላክቷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute