የኤ.አይ ሥርዓትን በማልማት ሕጋዊ ያልሆነ ገንዘብን ለመከላከል እና ለሽብርተኝነት ድጋፍ የሚውል ገንዘብን ለመቆጣጠር የሚያስችል ስምምነት ተካሄደ።
· MOU
The Ethiopian Artificial Intelligence Institute and the Financial Intelligence Service have signed a partnership agreement to develop an AI-powered system aimed at proactively detecting money laundering and preventing terrorism financing.
ስምምነቱ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና በፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መካከል የተፈረመ ነው።
ይህ ስምምነት ሕጋዊ ያልሆነ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ለማቅረብ የሚደረግ ሂደትን ቀድሞ በመለየት ለመከላከል እንዲሁም ለሽብርተኝነት ድጋፍ የሚውል ገንዘብን ለመቆጣጠር የሚያስችል የኤ.አይ ስርዓትን ለማልማት ያለመ ነው።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የስምምነቱ ዓላማ የሀገራችንን የፋይናንስ ዘርፍ ደህንነት ማስጠበቅ እነደሆነ ገልፀዋል። ዋና ዳይሬክተሩ በአሁኑ ወቅት የፋይናንስ ወንጀሎች እየረቀቁ በመምጣታቸው አደጋ ሳያደርሱ አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል ዓለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኤ.አይ ስርዓት በማልማት ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮችም እንዲጠቀሙበት እናደርጋለን ብለዋል፡፡
የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ በበኩላቸው ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ውስብስብ በመሆኑ በኤ.አይ የታገዘ ስርዓት ማልማት ወንጀሉን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ ሲስተሙን በሀገራችን በማልማት በአፍሪካ ግንባር ቀደም ሀገር መሆናችንንም አቶ ሙሉቀን አማረ አብራርተዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute