የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ኢንስቲትዩቱን ጎበኙ።
· Visiting
Oromia Insurance Explores AI Partnership with EAII to Enhance Digital Services, Customer Experience, and Operational Efficiency
የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልዑክ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የስራ ጉብኝት አድርጓል። በኢንስቲትዩቱ እየተከናወኑ ያሉ የቴክኖሎጂ ልማት እና የምርምር ስራዎችን የሚመለከት ማብራሪያ ለልዑካን ቡድኑ ቀርቧል።
የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ቺፍ ሪሶርስ ኦፊሰር አቶ ሳሙኤል ተስፋ ኩባንያቸው በዘርፉ ያለውን የአሰራር ቅልጥፍና ለማሳደግና የአገልግሎት አሰጣጡን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የደንበኞችን እርካታ ለመጨመር እና የኩባንያውን ተደራሽነት ለማስፋት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የታገዙ አሰራሮችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት አቶ ሳሙኤል ይህንን እውን ለማድረግም በሁለቱ ተቋማት መካከል በጋራ መስራት የሚቻልባቸው ሁኔታዎች እንደሚመቻቹ ተናግረዋል።
የልዑካን ቡድኑ በኢንስቲትዩቱ ቆይታው የኤ.አይ ስታርትአፕ ማዕከልን፣ ዲጂታል ቤተ-መጽሐፍትን፣ የምርት ማሳያ ክፍልን እና የሮቦቲክስ ወርክሾፖችን
ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከበርካታ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ ሲሆን በቀጣይም ይህንን መሰል የአጋርነት ስራዎቹን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute