የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መሥሪያ ቤት ጉብኝት አድርጓል፡፡
· Visiting
“አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በሀገራችን በብዙ መስኮች ወደ ትግበራ እንድንቀይረው የሚያስችል አቅም እንደተገነባ በጉብኝታችን አስተውለናል፡፡” የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ
የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መሥሪያ ቤት ጉብኝት አድርጓል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ለሥራ ኃላፊዎቹ ገለፃ አድርገዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ በገለፃቸው በምርምር፣ በትምህርት እና ስልጠና ችግር ፈቺ የኤ.አይ ቴክኖሎጂዎችን በማልማት በኢንስቲትዩቱ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በበኩላቸው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በሀገራችን በብዙ መስኮች ወደ ትግበራ እንድንቀይረው የሚያስችል አቅም እንደተገነባ ተመልክተናል ብለዋል፡፡ በጉብኝታቸውም በኢንስቲትዩቱ የተሰሩ ስራዎች ተቋሙ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ መስክ ረጅም ርቀት እንደተጓዘ ምስክር መሆናቸውን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute